መሠረቱ የተናጋ ስርዓት ፣ መጨረሻው ሃገር እስከ ማፍረስ ይደርሳል።
top of page
  • jwbo430w

መሠረቱ የተናጋ ስርዓት ፣ መጨረሻው ሃገር እስከ ማፍረስ ይደርሳል።

መሠረቱ የተናጋ ስርዓት ፣ መጨረሻው ሃገር እስከ ማፍረስ ይሆናል።

*የኢትዮጵያ ኢምፓየር (ኢትዮጵያ ሃገረ ምስረታ) ከጅማሬው ጨቋኝና ተጨቋኝ ስርዓት በመሆኑ፣ህዝቦችና ብሄሮችን ገባርና አስገባሪ፣ጌታና ሎሌ አድርጎ በመነሳቱ የመጀመርያው የሃገረ ምስረታ ውድቀት ነው።



*ቀጥሎም፣የብሄሮችን ሉዓላዊነትና የህዝቦችን ነጻነት በጠመንጃ ደፍቆ ኢምፓየሩን ስላስቀጠለ መንግሥትና ህዝቦች፣ብሄርና ብሄሮች መሃል የተሳካ መስተጋብር እንዳይፈጠር ትልቁን ሚና ተጫውቷል።

ይህም አልበቃ ሲል፣ለነጻነትን፣ለፍትህና እኩልነት የሚታገሉትን ሃይሎች በፖለቲካ መድረክ ከመፍታት ይልቅ ፣ በሃይል ለማጥፋት መንግስታቶች ሲወስዱ የነበረው እርምጃ፣ወደ ለየለት የህዝብ ቁጣና አመጽ መገፋፋቱን በተጨባጭ መሬት ላይ ያለ ሃቅ ሆኖ እንመለከታለን።


*የኦሮሞ ህዝብ ለዘመናት መፍቱና ነጻነቱን ሲነፈግ የቆየ ከመሆኑ፣ከሌሎች ጭቁን ህዝቦች ጋር በመተባበር፣ የኢትዮጵያ ስርዓትን ሲታገልና ለመቀየርም ሲሞክር ዛሬን ደርሷል። ሆኖም በየግዜው ስልጣኑን የምይዙ መንግሥታቶች፣በየተራ የኦሮሞን ህዝብ ሲገሉ፣ሲያስሩ፣ከቄዬው ሲያፈናቅሉ፣መሬቱን ሲቀሙ፣ቋንቋውን ሲገድቡ፣ከሃገር ሲያሳድዱና እንደ ሁለተኛ ዜጋ ሲመለከቱት፣በልጆቹ ደም ያመጣውን ትግል ሲቀሙና ሃብቱን በየተራ ሲዘርፉ የበይ ተመልካች ሆኖ ሲኖር መክረሙ፣ግፍን መሸከም አቅም ያጣበት ዘመን ላይ ደርሷል።


*የብልጽግና መንግሥት ከኢህአዴግ ተነጥሎ ስልጣን ከያዘበት እለት ጀምሮም፣የኦሮሞ ህዝብ ከየትኛውም ብሄርና ህዝብ በላይ፣የመንግስት ጥቃት ሰለባ ሆኗል! ይህን እወነታና መሬት ላይ የሚታይን ሃቅ መቀበል ያተሳናቸው ወገኖች፣ይህን ህዝብ እንዳልተበደለና ስልጣን ላይ ያለው የወመኔ ስብስብ ተወካዩ አድርገው "የኦሮሙማ መንግሥት" ሲሉ በትዝብት እንመለከታለን። አልፎም፣ከኦነግ ሰራዊት (ኦነሠ) የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከስርዓቱ ጋር የሚያደርገውን የነጻነት ትግልን "የወንድሜቾች ጦርነት" የሚል የትርክትና ድርሰት፣ሲጽፉና ሲናገሩም እናያለን። በመሰረቱ የኦሮሞ ህዝብ ገግለሰቦች ወይም ከሌሎች ሃይል ጋር ሳይሆን፣ከስርዓቱ ጋር ያለው የነጻነት ትግልና ኢፍትሐዊ ከሆነ ስርዓት ማሃል የሚደረግ ትግል ነው።

ኢፍትሐዊነት እስካለ፣ ያለህዝቦችና ብሄሮች ፍቃድ የተመሰረተው ኢምፓየር እስካልተስተካከለ፣እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብቱን በህገ-መንግስቱ መሠረት ካልተረጋገጠ፣የኦሮሞ ህዝብ ትግሉን ባልተቋረጠና በሁለገብ መልክ የሚቀጥል ይሆናል።

41 views0 comments
                 Ejeensii Burqaa Oduu Jaarmiyaa Waraana Bilisummaa Oromoo Waliigalaa(EBO-JWBOW)
                                  General Organazation of the  Oromoo Liberation Army  (GOOLA)
bottom of page